የቤተ–መጽሀፍቱ ተገልጋዬች
- የከተማው ብሔር ብሔረሰቦች፣
- ዘር ፆታ ፣ እድሜ ፣ ቀለም ሀይማኖት ፣ የትምህርት ደረጃ ሳይለይ የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎች/ህዝቦች፣
- የሚመለከታቸው ተማሪዎችና ተገልጋዬች፣
- የምርምርና ትምህርት ተቋማት፣
- ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች፣
- የመንግስት ሠራተኞች፣
- አጥኝና ተመራማሪዎች፣
የተገልጋዬች መብቶች
- በቤተ መጽሀፍቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን የማግኘት መብት (በተቀመጠው የአገልግሎት ስታንዳርድ መሠረት በክብር የመስተናገድ)፣
- መረጃ የማግኘት መብት፣
- በቤተ መጽሀፍቱ አሰራር ላይ አስተያየትና ቅሬታ የማቅረብና ፈጣን ምላሽ የማግኘት መብት፣
- በቤተ መጽሀፍቱ የዕቅድ ዝግጅት፣ የአፈፃፀምና ግምገማ ሂደቶች ላይ የመሳተፍ፣
- የውሰት፣የንባብ፣የተፈቀደለት ቅጅ የመውሰድ/በዋስ አማካኝነት፣
- በመጻህፍትና ሌሎች የቁሳቁስ ግዥዎች ላይ መሳተፍ፣
ለቤተ-መጽሀፍት እድገትና መሻሻል ገንቢ ሀሳቦችን መስጠትና በገንዘብ፣ በማቴሪያል ፣ በሙያ መደገፍ፡፡
ለተገልጋዮቻችን የምንገባው ቃል
- ተገልጋዬቻችንን በቅንነትና በታማኝነት እናገለግላለን፣
- ፍትሃዊ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት እንሰጣለን፣
- ያቀድናቸውን እቅዶች በተገቢው መንገድ በወቅቱ እንፈጽማልን፣
- ደንበኛ ንጉስ መሆኑን አውቀን ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት እንሰጣለን፡፡
በቤተ–መጽሀፍቱ የሚሠጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- በቤተ-መጽሃፍቱ ለሚስተናገዱ ደንበኞቻችንን ቤተ-መጽሃፍቱ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በስራ ሠዓትና እንዲሁም ቅዳሜ ጧት ከ2፡30 እስከ 6፡30 ሠዓት ክፍት መሆኑን እየገለጽን፡-
- በአስተያየት የቀረቡ ሂስና ገንቢ ሀሳቦችን ገምግሞ ምላሽ መስጠት፡፡
- አጠቃላይ የንባብ አገልግሎት መስጠት፡፡
- የውሰት አገልግሎት መስጠት፡፡
- የመረጃ አገልግሎት፡፡
- ቤተ-መጽሀፍት የማስተዋወቅ ስራ፡፡
- የኢንተርኔት አገልግሎት፡፡
- ፎቶ ኮፒ አገልግሎት፡፡
- ስለ ቤተ-መጽሀፍት የወጡ መመሪያዎችን ደንቦችንና አዋጆችን ለማወቅ ለሚፈልጉ አካላት ጥያቄ ምላሽ መስጠት፡፡
- አባላትን መመዝገብ፡፡
- አንድ ደንበኛ ለአስር ቀን የሚፈልገውን መጽሃፍት ይዋሳል ከአስር ቀን ውጭ ካሳለፈ ግን 1ብር ይቀጣል፣ መጽሀፍ ከጠፋበት ደግሞ የመጽሃፉን ዋጋ እጥፍ ይከፍላል፡፡
- ሠራተኞች ለ15 ቀን ይዋሣሉ አንብበው ይመልሳሉ ከጠፋባቸው የመጽሃፉን ዋጋ እጥፍ ይከፍላሉ፡፡
የቤተ መጽሃፍት ደንቦች /ሕጐች/
- የቤተ-መጽሀፍቱን ሀላፊ ወይም ሠራተኛ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር በስራው ላይ እያለ ማነጋገር አይፈቀድም፣
- ለአንባብያን ወደ አልተፈቀደ የቤተ-መጽሀፍት ክፍል መግባት ክልክል መሆኑን ማወቅ፣
- ከቤተ-መጽሀፍቱ በስተቀር በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ማስታወቂያ ወይም ማንኛውንም ጽሁፍ መለጠፍ አይቻልም፣
- ማንኛውም አንባቢ ከመደርደሪያው ላይ አንስቶ ያነበበውን መጽሀፍ ቦታው መመለስ ይጠበቅበታል፣
- ተመሳሳይ ንብረት ይዞ መግባት ክልክል ነው፡፡ሁለት ሽፋን የሌለው ማስታወሻ/ደብተር መያዝ፣
- ጐን ለጐን ማውራት መወያየት አንባቢን የሚያውክ ከፍ ያለ ድምጽማሰማት አይገባም፣
- የሚጮህ ጫማ አድርጐ መግባት፣
- ማንኛዉንም ወረቀት መቅደድ፣
- ጋቢ & ካፖርት & ቦርሳ & ኮፍያ፣ሻሽ አድርጐ መግባት፣
- ወንበር ጠረንጴዛ ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ፣
- የተጠቀሙበትን መጽሃፍት ከቦታው ውጭ ማስቀመጥ ወይም በጠረንÆዛ ላይ ትቶ መውጣት፣
- ቤተ-መጽሀፍቱ ውስጥ መብላትና መጠጣት አይፈቀድም፡፡
- ሞባይል/ተንቀሳቃሽ ስልክ ድምፅ ማጥፋት/ሣይለንት ማድረግ፣
- ካፖርት ሻሽ፣ ጋቢ፣ ኮፍያ፣ ማድረግና ሽቶ፣ ቅቤ፣ የመሳሰሉትን ነገሮች አለመጠቀም፡፡
- የቤተ-መጽሀፍቱን እቃ ወይም ንብረት ማቆሸሽ፣ መቅደድ፣ መቁረጥ፣ ማበላሸት፣ መስበርና ማጥፋት በሀላፊነት ያስጠይቃል፡፡
- የሌላውን ሠው መዋሻ ካርድ ይዞ ለመዋስ መሞከር፣
- ሌሎች ያልተጠቀሱ የተገልጋዩችን መብት የሚጋፋ ነገሮች ማድረግ፣
- ከሠራተኞች በቀር ወደ አልተፈቀደ ክፍል መግባት ክልክል ነው፣
- ማንኛውም ተጠቃሚ በተጠየቀ ግዜ መታወቂያ ማሳየት አለበት፡፡
በቤተ መጽሀፍቱ የሚሰጡ የመረጃ አይነቶች
- በመረጃ ክፍል ውስጥ የሚሰጥ አገልግሎት፡-ተጠቃሚዎች ሊያገናዝቡ የሚፈልጉትን መረጃ በቀጥታ የሚያገኙበት ነው፡፡
- የመረጃ ንባብ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በተለያዪ ጉዳዪች ላይ በግንባር በመቅረብ ፣ በስልክ ፣ በደብዳቤ ወ.ዘ.ተ የሚያገኙበት ሲሆን ለምሌ፡- ለሚሰራው ስራ የሚያግዙ የመጽሀፍት ዓይነቶችና ዝርዝር፣ለማወቅ የሚፈለገውን ነጥብ በአጭር አገላለጽ በጽሁፍና በቃል ወ.ዘ.ተ ግልጋሎት የሚገኝበት ነው፡፡
- አጠቃላይ የመረጃ አገልግሎት፡-ስለ ቤተ-መጽሀፍቱ አጠቃቀም ፣ የካታሎግና የክላስፊኬሽን አጠቃቀም ማስረዳት፣መጽሀፍት በሸልፍ ላይ ያሉበትን ቦታ መጠቆም፣ ስለ አነባበብ ዘዴዎች ማስረዳት፣ለአዲስ ተጠቃሚ ስለ ቤተ-መጽሀፍቱ አጠቃቀም ማስረዳት ናችው፡፡
መረጃ ማሰተላለፊያ ዘዴዎች
- ወቅታዊ መረጃዎች፡– በኢንተርኔት ፣ በፖስታ ቤት ፣ በመረጃ ማዕከል ፣ በአካል ፣ በስልክ….
አድራሻ፦
- ስልክ ፦ 033 111 84 04/ 033 111 8535/ 033 111 66 92
- ፋክስ ፦ 033 111 46 14
- ፖስታ፦ 1460